Ete Emete - Part 1 (Kana TV Drama)

286 Views
Published

Ete Emete - Part 1 (Kana TV Drama).

ታህሳስ 27፣2017

 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከሚገኙ አቅመ ደካሞች መከከል 100ዎቹ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ የሚያስችል ፕሮግራም ተጀመረ። 

 

ለአቅመ ደካሞቹ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ ማድረግ የጀመረው ፖል ፎቶ ቬሎና ሜክአፕ ነው። 

 

ጅርጅቱ ሃያ ሁለት አካባቢ በሚገኘው መስሪያ ቦታው በየቀኑ 100 ሰዎችን ለሶስት ወራት ለመመገብ የሚያስችል መርሀ ግብር በትናንትናው  ዕለት አስጀምሯል። 

 

ድርጅቱ ይህንን ለማድረግ ያሰበው "ወገኔ ሳይበላ አልበላም" በሚል ሀሳብ ማህበረሰባዊ ሀላፊነት ለመወጣት አስቦ መሆኑን የድርጅቱ ባለቤት ወጣት ጳውሎስ ጎይቶም ተናግሯል። 

 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ነዎሪ ከሆኑት ውስጥም 150 ዎቹ ለበዓል መዋያ ዘይትና ዱቄት ተሰጥቷቸዋል። 

 

በትናንትናው ዕለት በይፋ በተጀመረውና ለሶስት ወራት የሚዘልቀው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብርም ሙሉ ወጪውን በፖል ፎቶ ቬሎና ሜክአፕ ይሸፈናል ተብሏል። 

 

ድርጅቱ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ የሚያደርጋቸው ሰዎችን ቁጥር የመጨመር እቅድ እንዳለውም የድርጅቱ ባለቤት ጳውሎስ ተናግሯል። 

 

በዝግጅቱ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Category
Etemete | እቴ እሜቴ
Be the first to comment