Kanadramas - Ethiopian Video Sharing
Welcome
Login / Register

አዲሱ አረጋ እና ሽመልስ አብዲሳ ከጌታቸው አሰፋ ጋራ ያደረጉት ምስጢራዊ ትንንቅ

ያልተሰሙ የ“ጀነራሉ” እና የ“አቢዶ” ገድሎች
➢ ቲም ለማ ላይ ግድያ ለመፈጸም በጌታቸው አዛዥነት የተሰማሩ ሁለት የደህንነት ባልደረቦችን ይዘዉ አስረዋል፡፡
➢ ጌታቸው አሰፋ በአስመላሽ እና አባዱላ አማካኝነት ፓርላማ ዉስጥ የቀበረውን ሴራ አክሽፈዋል፡፡
➢ ታዋቂውን ድምጻዊ ኃጫሉ ሁንዴሳን ከሚሊኒየም አዳራሽ ከደህንነቶች መንጋጋ አስመልጠዋል፡፡
➢ ጌታቸው አሰፋ የሽመለስ አብዲሳ ሰርግ ላይ ድንኳን ሰብሯል፡፡


በቅርቡ የኦሮምያ ክልል በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮምቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና እና አቶ አዲሱ አረጋ በቅርብ ጓደኞቻቸዉ የሚጠሩት “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” በሚሉ ቅጽል ስማቸዉ ነዉ፡፡ ሽመልስ “ጀነራሉ” በሚል ቅጽል ስም የወጣለት ቆፍጣና እና ቆጣ ቆጣ እያለ አመራር ስለሚሰጥ እና በዉጤት የሚያምን ስለሆነ ሲሆን አዲሱ ደግሞ ፈጣን፣ ሪስክ የማይፈራ እና የዉሳኔ እና የድርጊት ሰዉ በመሆኑ በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ያገለግል በነበረበት ይሰጣቸዉ በነበሩት ድፍረት የተሞላባቸዉ መግለጫዎች “አቢዶ” የሚል ቅጽል ስም ከትግል አጋሮቹ አሰጥቶታል፡፡በአፋን ኦሮሞ “አቢዶ” ማለት “እሳቱ” ማለት ነዉ፡፡ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና በቅርቡ የመለካከያ ሚኒስትር የሆኑት ኦቦ ለማ ሁለቱን ሲጠሯቸው “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” እያሉ እንጂ የሚጠሯቸው ጠርተዋቸው አያውቁም፡፡
ሽመልስ አብዲሳ እና አዲሱ አረጋ ፍጹም የማይለያዩ ተመሳሳይ ዝንባሌ ያላቸዉ፣ እጅግ በጣም በድፍረት የተሞሉ ወጣቶች እንደሆኑ እና ቅርበታቸዉም ከጓደኝነት ያለፈ ፍቅራቸዉም ከወንድማማቾች በላይ እንደሆነ በቅርብ የሚውቋቸው ሰዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡ በፓርቲዉ አባላት ዘንድም በስነ ምግባርም ሆነ በአመራር ብቃታቸዉ የተመሰከረላቸዉ በፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ተስፋ እና ዕምነት የተጣለባቸዉ ትንታግ ታጋይ ወጣት ምሁራን ናቸዉ፡፡ ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ ቢባል ማጋነን አይሆን፡፡ ፈጽሞ አይለያዩም፡፡ ለአብነትም በጅማዉ ጉባዔ የኦዲፒዉ ሊቀመንበር ዶ/ር አቢይ ሁለቱም አንድ መሆናቸዉን ለማሳየት በስብሰባዉ ወቅት ዕድል ሲሰጣቸዉ የአባታቸዉን ስም በማቀያየር ሲጠራቸዉ እንደነበረ አይተናል፡፡ ሽመልስን “ሽመልስ አረጋ”፣ አዲሱን ደግሞ “ አዲሱ አብዲሳ” እያለ ሲጠራቸዉ ነበር፡፡ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ለማለት ነዉ፡፡
ፍልሚያ -1 -
“በጀነራሉ” እና “አቢዶ” አሸናፊነት የተጠናቀቀው በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው ፎርሙላ 1 የመኪና ሽቅድድም ውድድር!!
በታህሳስ ወር 2010 የ17 ቀናቱ የኢህአዴግ ስብሰባ በተካሄደበት ወቅት ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዉ በጥብቅ የመረጃ እና የደህነነት አባላት ጥብቅ ክትትል ስር ወድቀዉ ነበር፡፡ የኦዲፒ ጽ/ቤት እና ፊላሚንጎ ያለዉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤትም በወታደሮች እና በከባድ መሳሪያ በስዉር ተከቦ ነበር፡፡ በተለየ ሁኔታ ክትትል ሲደረግባቸዉ ከነበሩት አመራሮች መካከልም ኦቦ ለማ መገርሳ፣ ዶ/ር አቢይ አህመድ፣ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ፣ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ አዲሱ አረጋ እና ሽመልስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡
በታህሳስ 2010 በአንዱ ቅዳሜ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም በከተሞች እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ተመልክተዉ ለክቡር ፕሬዝዳንቱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የክልሉ አመራሮች የስራ ስምሪት ይሰጣቸዋል፡፡
“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ም ከገላን እስከ አዳማ ከተማ ያለዉን እንቅስቃሴ በመስክ ተመልክተዉ ሪፖርት ለማቅረብ ተቀጣጥረዉ በሌሊት ይገኛሉ፡፡ እንደ ተለመደዉም በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሰሩ በኋላ ቁርሳቸዉን ተመግበዉ፣ የ“አቢዶ”ን ተሸከርካሪ ኦዲፒ ጽ/ቤት አቁመዉ በ“ጀነራሉ” አሽከርካሪነት፣ በ“ጀነራሉ” መኪና ጉዟቸዉን ወደ አዳማ ይጀምራሉ፡፡ ገላን ከተማ ደርሰዉ ያለዉን ዝግጅት በአጭሩ ጎብኝተዉ ወደ ዱከም ዘለቁ፡፡ በቲም ጌታቸው አሰፋ በቀጥታ ትዛዝ የሚመሩት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት ዉብሸት ላዉጋዉ እና ለጊዜው ስሙን የረሳሁት ሰው ብርማ ቀለም ባላት ቶዮታ ኮሮላ መኪና የቲም ለማ አባላት የሆኑትን “ጀነራሉ” እና “አቢዶ”ን በቅርብ ርቀት ይከታተሏቸው ያዙ፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ዱከም የነበረዉን ዝግጅት በአጭሩ ከቃኙ በኋላ ምሳቸዉን በወቅቱ የከተማዉ ከንቲባ ኦቦ ጀባ አዱኛ ጋባዥነት ተመግበዉ ጉዞአቸዉን ወደ ቢሾፍቱ ቀጠሉ፡፡ በገቡበት እየገባች፣ በቆሙበት ስትቆም የነበረችዋ ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ አሁንም በቅርብ ርቀት መከታተሏን ቀጥላለች፡፡እነርሱ ግን ክትትል ስር መሆናቸዉን ልብ ሳይሉ እየሳቁ እየተጫወቱ ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡ የቢሾፍቱ ጉብኛተቸዉን ጨርሰዉ ወደ ሞጆ እያቀኑ እያለ “ጀነራሉ” በስፖኪዎ ደጋግሞ ከኋላ የምትከተላቸዉን ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ መኪና ማየቱ በውስጡ ጥርጣሬ አሳድሮበታል፡፡ “አቢዶ” ጋቢና ሆኖ የተለመደ ቀልድ እና ጨዋታዉን ቀጥሏል፡፡ “ጀነራሉ” ክትትል እየተደረገባቸዉ መሆኑን ቢጠራጠም ዝም ብሎ መኪናዉን ወደ ፊት መንዳቱን ቀጠለ፡፡ ለ“አቢዶ” ምንም ነገር አልነገረዉም፡፡ ጉዙአቸዉን ቀጥለዉ ሞጆ ደረሱ፡፡ ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ ኮሮላዋ አሁንም ከኋላቸዉ ናት፡፡ የሞጆ ጉብኝታቸዉን ለመቀጠል ወደ ሰፈር የዉስጥ ለዉስጥ የሚያስገባ መንገድ ሲይዙ ኮሮላዋ አልፋቸዉ ሄደች፡፡ “ጀነራሉ” ም የአጋጣሚ ጉዳይ እንጂ ክትትል እየተደረገባቸዉ እንዳልሆነ በማመን ጉዞዉን ቀጠለ፡፡ የሞጆ ጉብኘት ተጠናቀቆ ወደ አዳማ ጉዞ ሲቀጥሉ ኮሮላዋ የፍጥነት መንገድ መግቢያዉ አካባቢ ቆማ ጠበቀቻቸዉ፡፡ ከኋላ ሆና ክትትሏን ቀጠለች፡፡ ጀነራሉ በተረጋጋ መንፈስ እየሆነ ያለዉን ነገር ለጓደኛዉ ሳይነግር ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ አዳማ ተፈተለከ፡፡ የአዳማዉ የመስክ ጉብኝትም በአጭሩ ተጠናቀቀ፡፡ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ፡፡ አሁንም ኮሮላዋ በቅርብ ርቀት አለች፡፡ አዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ ሲገቡ ጀነራሉ መኪናዉን በ180 ፍጥነት አስወነጨፋት፡፡ኮሮላዋ በፍጥነት ለመከታተል ብትሞክርም ከጄኔራሉ የማሽከርከር ብቃት እና የጄኔራሉ ዘመናዊ ተሸርካሪ ጉልበት ጋር እኩሉ መራመድ ስላልቻለች የአቅሟን ሁሉ ሞክራ ወገቤን አለች፡፡ ጀነራሉ ቱሉ ዲምቱ ሲደርስ በጎሮ መንገድ መሄድ ሲገባዉ በለቡ በኩል ጉዞዉን ቀጠለ፡፡ አዲስ አበባ ሲደርስ ኮሮላዋ ከኋላ አለመኖሯን አረጋገጠ፡፡ ጀነራሉ “ደህንነቶች ሲከታተሉን ነበር፡፡ ጎበዝ ሾፌር በመሆኔ በፍጥነት ቀድሜአቸዉ አስመለጥኩህ፡፡ አንተ መኪናዉን የምተነዳ ቢሆን ኖሮ አስበልተኸን ነበር” ብሎ ለአቢዶ ይነግረዋል፡፡ ሁለቱም ነገሩን እያብሰለሰሉ፣ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸዉ እየተመካከሩ አዲሱ መኪናዉን ወዳቆመበት ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት ፊት ለፊት ወደ ሚገኘዉ የኦዲፒ ጽ/ቤት ግቢ ይደርሳሉ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ተሰነባብተዉ አዲሱም የራሱን መኪና አስነስቶ ሽመልስን ተከትሎ ከግቢዉ ይወጣሉ፡፡ ከግቢዋ እንደወጡ የሽመልስ አይን ኮሮላዋ መኪና ላይ ያርፋል፡፡ መኪናዋ በጎሮ በኩል ቀድማ መጥታ የኦዲፒ ግቢ አጥር ታካ ወደ ሳሪስ ፊቷን አዙራ ቆማለች፡፡ ሽመልስ ትንሽ አለፍ ካለ በኋላ የኋላ ማርሽ አስገብቶ መንገዱን ዘጋባት፡፡አዲሱም ከኋላ ደርሶ መኪናዋ እንዳንትቀሳቀስ በሚያደርግ መልኩ መንገዱን ዘጋዉ፡፡ ሽመልስ በፍጥነት ከመኪናዉ መዉረዱን ያዩ የደህንነት መስሪያቤቱ ባልደረቦች የሚካናቸዉን መስታወት ወደ መዝጋት ተጣደፉ፡፡ ሽመልስ ሽጉጡን በቀኝ እጁ ይዞ በግራ እጁ የመኪናዋን በር በማንኳኳት “ለምንድነዉ የምትከታተሉን ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ የሁለቱም ደህንነቶች ትኩረት ወደሱ ሆነ፡፡ ሁለቱም “እኛ እየተከታተልናቸሁ አይደለም፡፡ጓደኞቻችን ጋር ለመዝናናት ወደ ሳሪስ እየሄድን ነዉ” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በቅጽበት አዲሱ ግራ በሾፌሩ መቀመጫ በኩል ደርሶ “ማንም ሰዉ እንዳይንቀሳቀስ፣ እጅ ወደ ላይ” የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የደህንነት ባልደረቦቹ እጃቸዉን ወደላይ ከማድረግ ዉጪ ሌላ አማራጭ አልነበራቸዉም፡፡ በዚህ መሃል የኦዲፒ ጽ/ቤት ጥበቃ ልዩ ሃይሎች ደርሰዉ የደህንነት ባልደረቦቹን ቁጥጥር ስር ያዉሏቸዋል፡፡
መኪናዋ ስትፈተሽም የአጭር ርቀት እና የረጅም ርቀት ራዲዮ፣ ገንዘብ፣ ድምጽ ማፈኛ የተገጠመላቸዉ ሽጉጦች ተገኙ፡፡ ሁለቱ የደህነነት ባልደረቦችን አዲሱ ከነመታወቂያቸዉ ፎቶግራፍ አንስቶ በማህበራዊ ሚዲያ እንዲጋለጡ አደረገ፡፡በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው ፎርሙላ 1 የመኪና ሽቅድድም ውድድርም “በጀነራሉ” እና “አቢዶ” አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ በመጨረሻም የጌታቸው አሰፋ ልጆች ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዉ ለ15 ቀናት ምርምራ ሲደረግባቸዉ ከቆየ በኋላ የደህንነት መስሪያ ቤቱ እና የፌዴራል የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ጫና ከእስር ተፈተዋል፡፡
ፍልሚያ -2-
በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው የቤት ውስጥ ( የፓርላማ) ፊልሚያ
በቲም ጌታቸው አሰፋ በኩል ተጠባቂ ተጫዋቾች፡- አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) እና አባዱላ ገመዳ ፤በቲም ለማ በኩል ተጠባቂ ተጫዋቾች፡- “ጀነራሉ” እና “አቢዶ”
“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ከደህንነቶች ጋር ግብ ግብ ገጥመዉ ባሰሩዋቸዉ ጥቂት ቀናት ዉስጥ፣ የታህሳስ ወሩ የኢህአዴግ የ17 ቀኑ ስብሰባ እጅግ ተፋፍሞ ቀጥሏል፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” የኢህአዴግ ምክር ቤት አባል ስላልነበሩ በስብሰባዉ አይሳተፉም ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ የአዴፓ እና የኦዲፒ አመራሮች በከፍተኛ መናበብ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረዉ የህወሃትን ካምፕ ትንፋሽ ማሳጣት ጀምረዋል፡፡ በዚህ መሃል በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ የነበረዉ መሰሪዉና አይነስዉሩ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) አንድ ተንኮል አስቦ ከጌታቸዉ አሰፋ ጋር ይመካከራል፡፡ የአዴፓ እና የኦዲፒ አመራሮች ህብረት ለመበተን ብሎም ትንፋሽ ለማሰባሰብ ብቸኛዉ መንገድ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ ስለምታገኘዉ ልዩ ጥቅምን የተመለከተ አጀንዳ መዘርጋት ግድ ነዉ ብሎ ከሌላው መሰሪ ጓዱ ጌታቸዉ አሰፋ ጋር ይመካከራሉ፡፡ ማክሰኞ ዕለት አባይ ነፍሶ የኢህአዴግ ስብሰባ አቋርጦ በመዉጣት “ኦሮሚያ ከፊነፊኔ ስለምታገኘዉ ልዩ ጥቅምን በተመለከተ በሚቀጥለዉ አርብ የፐብሊክ ሂሪንግ ስለሚኖር እንድትገኙ” የሚል ደብዳቤ ይበትናል፡፡ በሚዲያም ያስነግራል፡፡ የአስመላሽ እና የጌታቸዉ አሰፋ ተንኮል የገባቸዉ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” አስቀድመዉ ወደ ስብሰባዉ የሚሄዱ ሰዎችን ማደራጀት እና መቀስቀስ ጀመሩ፡፡ አርብ እለት በጠዋትም ፓርላማ ገብተዉ የኦዲፒ እና የክልሉን መንግስት አቋም በግልጽ አስቀምጠዉ“ የጉዳዩ ባለቤት የኦሮሞ ህዝብ ሳይወያይበት እና ፍላጎቱን ሳይገልጽ፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሳይቋቋሙ ፐብሊክ ሂሪንጉ መካሄድ የለበትም ” ብለዉ ሽንጣቸዉን ገትረዉ ተከራከሩ፡፡ ከኦዲፒ እና ከአዴፓ የፓርላማ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ በማግኘታቸውም የእነ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) ሴራ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ፡፡ በ“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ተግባር የተበሳጨው ጌታቸው አሰፋ ለጊዜው ስብሰባውን በሻይ እረፍት እንዲቋረጥ በማድረግአባይ ነፍሶ እና አባ ዱላ በጌታቸዉ አሰፋ ትዕዛዝ ጉዳዩን አረጋተዉ ስብሰባዉን እንዲያስቀጥሉ በጌታቸዉ አሰፋ ተላኩ፡፡ አባዱላም አስመላሽን ጎትቶ እየመራ ወደ ፓርላማ አዳራሽ መጥቶ ቁጣ እና ተግሳጽ አወረደ፡፡ሁለቱን ልጆች ነቀፈ ዘለፈ! “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ወይ ፍንክች ብለዉ በአቋማቸዉ ጸኑ፡፡ እስከ ምሳ ሰዓትም ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻም ፓርላማዉ እንዲበተን አደረጉት፡፡ የሻይ እረፍቱ ላይ የአዴፓ አባላትን ሎቢ በማድረግ ከኦዲፓ አባላት ጋር የመከፋፈል ስራ ለመስራት የተሞከረውም ሳይሳካ ቀረ ፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ታላቅ ጀብዱ ባይፈጽሙና ይህን ለዘመናት የሚያስመሰግናቸውን አኩሪ ተግባር ባይከውኑ ኖሮ የአዴፓ እና የኦዲፒ ጥምረት እና መናበብ ገድል ይገባ ነበር፡፡ የ17 ቀኑ ስብስባ ላይ የታየውም የአዴፓ እና የኦዲፒ ጥምረትም የፓርላማው ቀጣይ ክፍል ነው፡፡አሁን የደረስንበትንም ለዉጥ በህወሃት ሴራ ምክንያት አናየዉም ነበር፡፡ፍልሚያ

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles

RSS